ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ
Waliya Capital Goods Finance Business S.C

የእኛ አገልግሎቶች

የዱቤ ግዥ

የዱቤ ግዥ የሚባለው አከራይና ተከራይ በሚያደርጉት ስምምነት መሰረት አከራይ በተወሰነ ጊዜ የሚፈጸም ክፍያ እየተከፈለው የካፒታል ዕቃ ተከራዩ እንዲጠቀምበት የሚፈቅድ አሰራር ነው፡፡ ኢንተርፕራይዙ ተመላሹን በከፈለ ቁጥር ተመጣጣኝ የባለቤትነት መብት እያገኘ ይሔዳል፡፡ መጨረሻም ክፍያውንና ተያያዥ ወጭዎችን ከፍሎ ካጠናቀቀ በኋላ የባለቤትነት መብቱን ያገኛል፡፡

የፋይናንሻል ኪራይ

የፋይናንሽያል ኪራይ ማለት ደግሞ ተከራዩ የኪራይ ስምምነቱ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ የካፒታል ዕቃውን በአግባቡ እንዲጠቀምበት የውል ስምምነት የሚገባበት ሲሆን ተከራዩ በካፒታል ዕቃው ላይ ምንም ዓይነት የባለቤትነት መብት የለውም፡፡ ክፍያውን ሲያጠናቅቅም መሳሪያውን ለአከራይ ይመልሳል ወይም ሁለቱ አካላት በሚያደርጉት ስምምነት መሰረት የተወሰነ ገንዘብ ከፍሎ ሊወስደው ይችላል፡፡

አገልግሎት የምንሰጥባቸው ዘርፎች

    ማኑፋክቸሪንግ

  • ጨርቃጨርቅና አልባሳት
  • እንጨትና ብረታ ብረት
  • አግሮፕሮሰሲንግ
  • ጨርቃጨርቅ እና ሹራብ
  • ቆዳና ቆዳ ውጤቶች
  • የህትመት እና የወረቀት ምርቶች
  • ኬሚካሎች እና የኬሚካል ምርቶች
  • የጎማ እና የፕላስቲክ ምርቶች
  • የማዕድን ውጤቶች

    ለግንባታ እና የግንባታ ግብአት ምርቶች

  • የግንባታ ግብዓት ማምረት(ጠጠር፣ ብሎኬት፣ ሴራሚክና ባዞላ እና ሌሎችንም)
  • የሚክሰርና ኮምፓክተር ስራ
  • ቁፋሮና ግንባታ ስራ

    ግብርና ሜካናይዜሽን

  • ለእርሻ፣
  • ለሰብልና ምርት መሰብሰብ
  • ለሌሎችም መሰል አገልግሎቶች

    አገልግሎት

  • ሕክምና አገልግሎት
  • ጉብኝት እና ቱሪዝም
  • ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች

ኢንተርፕራይዞች አገልግሎቱን ለማግኘት ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች እና ቅድመ ሁኔታዎች

  • በአክሲዮን ማህበሩ አገልግሎቶች ላይ ሙሉ ግንዛቤ ያላቸው፤
  • ስለሚጠይቁት መሳሪያ አጠቃቀም በቂ ክህሎት/ግንዛቤ ያላቸው
  • እንዲገዛ የሚጠየቀው የካፒታል ዕቃ የገንዘብ መጠን ከ25 ሽ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ብቻ የሆነ፤
  • የንግድ ስራ ዕቅድ /Business Plan/፤ ለትልልቅ ፕሮጀክቶች ፕሮፖዛል ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ለሚገዛላቸው ማሽን ዝርዝር መግለጫ /Specification/ የሚያቀርቡ፤
  • እንዲገዛላቸው የሚፈልጉትን የካፒታል ዕቃ ጥቅል ዋጋ ከ20 እስከ 50 በመቶ ቅድመ ቁጠባ መቆጠብ የሚችሉ፤
  • የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  • መሰረተልማቱ የተሟላ በቂ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ያላቸው
  • ከአበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት የመልካም ተበዳሪነት ታሪክ ያላቸው፤
  • ለነባር ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ መዝገብ ያስመረመሩ፤ አዲስ ከሆኑም ለማስመርመር ፍቃደኛ የሆኑ፤
  • ለሚቀርብላቸው መሳሪያ የመድህን ሽፋን (የጉዞ እና የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ) የሚገቡና በየአመቱ ለማሳደስ ፈቃደኛ የሆኑ፤
  • መሳሪያውን በውል ለማስመዝገብ ፈቃደኛ የሆኑ፤
  • መሳሪያውን የሚንከባከቡና ብልሽት ሲያጋጥም የሚያስጠግኑ እንዲሁም ጥበቃ የሚያደርጉ፤
  • የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ያላቸው /ብድር ማግኘት የሚችሉ፤
  • የጋብቻ ሁኔታን (ያገቡ /ያላገቡ) የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ
  • በሚኖሩበት ቀበሌ/ክፍለ ከተማ/ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ቅድሚያ በሚሰጣቸው የስራ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ኢንተርፕራይዞች ከሆኑ በፈጻሚ አካላት በጋራ ተመልምለው የማምረቻ መሳሪያ ኪራይ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

ተልዕኳችን ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ዘመናዊ ሁሉን አቀፍና ቀልጣፋ የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ለአገሪቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው።

እኛ ማን ነን?

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ/ማ በመጀመሪያ በካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ስራ አዋጅ ቁጥር 103/1990 ዓ.ም መሰረት እንደገናም በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 807/2005 ዓ.ም መሰረት የተቋቋመ የፋይናንስ ተቋም ነው፡፡ የንግድ ፈቃድ የተሰጠው በ2006 ዓ.ም አጋማሽ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ሲሆን የኦፕሬሽን ተግባሩን የጀመረው በ2007 ዓ.ም አጋማሽ ነበር፡፡ ይህም በሀገራችን ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው በሚያስቀምጠው የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂው መሰረት ነው፡፡ ይህም መሬት ላይ እንዲያርፍ ከሚያስችሉ ቁልፍ ተቋማት መካከል የማንፋክቸሪንግ ዘርፉን የሚያግዙ የፋይናንስ ተቋማትን ማደራጀትና ማጎልበት አንዱ በመሆኑ ነው፡፡

አክሲዮን ማህበሩ በዋና መስሪያ ቤት እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደረጃ መዋቅራዊ አደረጃጀቶች እንዲኖሩት ተደርጎ የተመሰረተ ተቋም ነው፤ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ በስራቸው የሚመሯቸውን ሳተላይት ጽ/ቤቶች ያጠቃልላሉ፡፡ በመሆኑም ዋናው መስሪያ ቤት በባህር ዳር ከተማ የሚገኝ ሲሆን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹን በተመረጡ ከተሞች ላይ በማድረግ የተደራጀ ነው፡፡ አሁን ላይ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትን ጨምሮ በ27 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር ባሉ 187 ሳተላይት ጽ/ቤቶች በአጠቃላይ በ214 ከተሞች ላይ ተደራሽ እየሆነ ነው፡፡

ተልዕኮ

ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ዘመናዊ ሁሉን አቀፍና ቀልጣፋ የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ለአገሪቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው።

ራዕይ

እ.ኤ.አ. በ2035 በኢትዮጵያ ካሉት የሊዝ ኩባንያዎች መካከል ግንባር ቀደም ሆኖ ማየት፤

ዕሴቶች

የዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ዋና ዋና እሴቶች

የላቀ አገልግሎት

አክሲዮን ማህበሩ ለደንበኞች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የማምረቻ መሣሪያዎች እና በጥናት የተደገፈ የላቀ አገልግሎት በማቅረብ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ አፈፃፀም ከፍተኛ ደረጃ ለማድረስ በቁርጠኝነት ይሰራል፤

ፈጠራን ማበረታታት

አክሲዮን ማህበሩ ለተጠቃሚዎች የሚቀርቡ የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎቶችን እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶችን የሚያሟሉ የፈጠራ ሀሳቦችንና አሰራሮችን በማዳበር ያስተዋውቃል።

ግልጽነት እና ተጠያቂነት

የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ለሚፈልጉ ለሁሉም ኢንተርፕራይዞች፣ አጋርና ባለድርሻ አካላት በአስተማማኝነት እና በመደበኛነት መረጃ የመስጠት፣የመከታተል፣ሪፖርት የማድረግ፣ የመገምገምና የግምገማ ውጤቶች ላይ ተመስርቶ በአ/ማህበሩ የሀብትና ንብረት አጠቃቀም ዙሪያ ግልጽነት እና ተጠያቂነት በተሞላበት አካሄድ መፈጸም፤ የካፒታል ዕቃዎችን በጥንቃቄ ማስተዳደርና አክሲዮን ማህበሩ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎትና ውሳኔዎች ግልጽነትና ተጠያቂነት መርህን በሚያሰፍን መልኩ መረጃ መስጠት፤

ታማኝነት እና ሀቀኝነት

የአክሲዮን ማህበሩ ሰራተኞች በታማኝነት፣ በፍትሃዊነት እና ሙያዊ ስነ- ምግባርን በተላበሰ መንገድ አክሲዮን ማህበሩ ላወጣቸው ህጎች እና ለደንበኞቹ ታማኝ መሆንና ደንበኞችን ሊጎዱ የሚችሉ ማንኛውንም ተግባራት አለመፈጸም እንዲሁም ደንበኞችን በመልካም ስነ ምግባርና ቅንነት በተላበሰ መልኩ አገልግሎት መስጠት፤

ደንበኛ ተኮር አገልግሎት መስጠት

የአክሲዮን ማህበሩ አመራሮችና ሰራተኞች ጥራት ያለው አገልግሎት ለደንበኞች በመስጠት እና ደንበኞችን በማክበር ስኬታማ እንዲሆኑ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ፤

ምላሽ ሰጪነት

የአክሲዮን ማህበሩ አመራሮችና ሰራተኞች ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ ደንበኞችን ካለምንም ልዩነት በፍጥነት ተቀብሎ ለማስተናገድ በቁርጠኝነት ማረጋገጥ ሲሆን ሀላፊነትን ለመወጣት የመጀመሪያው እርምጃ ደንበኞችን አክብሮ መገኘት እና አንድ ደንበኛ ወደ ቢሮ ወይም ተቋማችን መጥቶ እርዳታ ሲጠይቅ አገልግሎት ሰጪው (የተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች) በአግባቡ ማዳመጥ እና ደንበኛው የሚፈልገውን በመረዳት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት።

በቡድን መስራት

የአክሲዮን ማህበሩ አመራሮችና ሰራተኞች አንድ የጋራ ተቋማዊ ግብ ላይ ለመድረስ ወይም አንድን ተግባር በጣም ውጤታማ እና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለማጠናቀቅ በጋራ ጥረት ውጤት ለማምጣት ቁርጠኝነትን ያመለክታል ።

ሙያዊ ስነምግባር

የአክሲዮን ማህበሩ ሰራተኞች ሥራውን በተሻለ ሁኔታ ለመስራት እና ዕድሎችን ለመጠቀም የሚያስፈልገውን እውቀት፣ ክህሎት፣ችሎታ እና ባህሪ ይዘው መገኘት ሲሆን በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እንኳን ሰራተኞች በመደቡ በተሰጣቸው ስራዎች ብቻ ሳይገደቡ ከተሰጣቸው የሥራ ዝርዝር ውጭ (በላይ) በመሄድ ያለማቋረጥ የአክሲዮን ማህበሩን ውጤት ለማሻሻል ጥረትን የሚጠይቅ ሂደት ነው።

የባለቤትነት ስሜት

ተነሳሽነትን የሚመለከት ሲሆን እኛ የአክሲዮን ማህበሩ ሰራተኞች ብቻ ሳንሆን ጠባቂና ባለቤትም ጭምር ነን፤ በጥሩ አፈጻጸም ተሸላሚዎችም መሆን እንችላለን ይገባናልም፤ በእያንዳንዱ ለውጥና መሻሻል እንደ ቡድን ወይም እንደ ግለሰብ እንደምንደሰት ሁሉ በእያንዳንዱ ብልሽትም በጋራ የሚቆረቁረን እና የሚቆጠቁጠን ልንሆን ይገባል፤ ይህ ማለት ሁላችንም የአክሲዮን ማህበሩ ዘብና ኦዲተሮች ነን።

ሞቶ

የደንበኞቻችንን እርካታ ለማረጋገጥ እንተጋለን።

መሪ ቃል

በኢትዮጵያ ተመራጭ የሊዝ ፋይናንስ ተቋም !

የዱቤ ግዥ አገልግሎቶች

የዱቤ ግዥ የሚባለው አከራይና ተከራይ በሚያደርጉት ስምምነት መሰረት አከራይ በተወሰነ ጊዜ የሚፈጸም ክፍያ እየተከፈለው የካፒታል ዕቃ ተከራዩ እንዲጠቀምበት የሚፈቅድ አሰራር ነው፡፡ ኢንተርፕራይዙ ተመላሹን በከፈለ ቁጥር ተመጣጣኝ የባለቤትነት መብት እያገኘ ይሔዳል፡፡ መጨረሻም ክፍያውንና ተያያዥ ወጭዎችን ከፍሎ ካጠናቀቅ በኋላ የባለቤትነት መብቱን ያገኛል፡፡

አገልግሎት የምንስጥባቸወ ዘርፎች

    ማኑፋክቸሪንግ

  • ጨርቃጨርቅና አልባሳት
  • እንጨትና ብረታ ብረት
  • አግሮፕሮሰሲንግ
  • ጨርቃጨርቅ እና ሹራብ
  • ቆዳና ቆዳ ውጤቶች
  • የህትመት እና የወረቀት ምርቶች
  • ኬሚካሎች እና የኬሚካል ምርቶች
  • የጎማ እና የፕላስቲክ ምርቶች
  • የማዕድን ውጤቶች

    ለግንባታ እና የግንባታ ግብአት ምርቶች

  • የግንባታ ግብዓት ማምረት(ጠጠር፣ ብሎኬት፣ ሴራሚክና ባዞላ እና ሌሎችንም)
  • የሚክሰርና ኮምፓክተር ስራ
  • ቁፋሮና ግንባታ ስራ

    ግብርና ሜካናይዜሽን

  • ለእርሻ፣
  • ለሰብልና ምርት መሰብሰብ
  • ለሌሎችም መሰል አገልግሎቶች

    አገልግሎት

  • ሕክምና አገልግሎት
  • ጉብኝት እና ቱሪዝም
  • ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች

ፋይናንሻል ኪራይ አገልግሎቶች

የፋይናንሽያል ኪራይ ማለት ደግሞ ተከራዩ የኪራይ ስምምነቱ ጸንቶ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ የካፒታል ዕቃውን በአግባቡ እንዲጠቀምበት የውል ስምምነት የሚገባበት ሲሆን ተከራዩ በካፒታል ዕቃው ላይ ምንም ዓይነት የባለቤትነት መብት የለውም፡፡ ክፍያውን ሲያጠናቅቅም መሳሪያውን ለአከራይ ይመልሳል ወይም ሁለቱ አካላት በሚያደርጉት ስምምነት መሰረት የተወሰነ ገንዘብ ከፍሎ ሊወስደው ይችላል፡፡

አገልግሎት የምንስጥባቸወ ዘርፎች

    ማኑፋክቸሪንግ

  • ጨርቃጨርቅና አልባሳት
  • እንጨትና ብረታ ብረት
  • አግሮፕሮሰሲንግ
  • ጨርቃጨርቅ እና ሹራብ
  • ቆዳና ቆዳ ውጤቶች
  • የህትመት እና የወረቀት ምርቶች
  • ኬሚካሎች እና የኬሚካል ምርቶች
  • የጎማ እና የፕላስቲክ ምርቶች
  • የማዕድን ውጤቶች

    ለግንባታ እና የግንባታ ግብአት ምርቶች

  • የግንባታ ግብዓት ማምረት(ጠጠር፣ ብሎኬት፣ ሴራሚክና ባዞላ እና ሌሎችንም)
  • የሚክሰርና ኮምፓክተር ስራ
  • ቁፋሮና ግንባታ ስራ

    ግብርና ሜካናይዜሽን

  • ለእርሻ፣
  • ለሰብልና ምርት መሰብሰብ
  • ለሌሎችም መሰል አገልግሎቶች

    አገልግሎት

  • ሕክምና አገልግሎት
  • ጉብኝት እና ቱሪዝም
  • ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች

የስልጠና አገልግሎት

ስልጠና ከአገልግሎቶቻን አንዱ ሲሆን አምራች ኢንተርፕራይዞች በተሻለ እውቀትና ክህሎት እንዲመሩ የሚያስችሉ የስልጠና አገልግሎት በተለያዩ አካላት እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ በተለይ የአክሲዮን ማህበሩን አገልግሎት ለማግኘት የሚመለመሉ ኢንተርፕራይዞች ለንግድ ስራ ውጤታማነት ከፍተኛ ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ስልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ለነባር ደንበኞችም የስራ ላይ ስልጠና የሚመቻችላቸው ሲሆን ለአብነትም ከአለም ባንክ እና ከሌሎች አብረውን ከሚሰሩ ተቋማትም በንግድ ስራ አመራር ጥበብ ላይ በተለያየ ጊዜ ስልጠናዎችን ያገኙ በርካታ ናቸው፡፡ ከዚህ ባሻገር በዘርፉ የተለያዩ አካላት ስልጠና ለመስጠት ሲፈልጉም ሙያዊ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡

    የስልጠና አገልግሎቶቻችን በመዋናነት በሚከተሉት ይዘቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

  • ሥለ ስራ አዋጭነት ጥናት፣
  • ስለንግድ ዕቅድ አዘገጃጀት፣
  • ሂሳብ መዝገብ አያያዝ፣
  • የማሽን አያያዝና አጠቃቀም፣
  • የስፔስፍኬሽን ዝግጅት፣
  • የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽ ድጋፍ (የቴክኒካል ክህሎት፣ የቴክኖሎጅ፣ የኢንተርፕረነርሽፕ እና የጥራትና ምርታማነት) በሚመለከት፤
  • በሴቶች አደረጃጀት፣ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት፣
  • ስለ ቁጠባ ጥቅምና አስፈላጊነት፣
  • ስለብድር አወሳሰድ አጠቃቀምና አመላለስ፣
  • የስራ ማስኬጃ ብድር አሰጣጥ ስልጠና ይሰጣል፡፡
  • እነዚህን ስልጠናዎች ከስራና ስልጠና ጽ/ቤቶች፣ ከሴቶች፤ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤቶች እና ከፀደይ ባንክ አ.ማ ጋር በመተባበር የሚሠጡ ሲሆን ተጠቃሚዎቹም የሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚ የሚሆኑ ደንበኞች ናቸው፡፡ በተጨማሪም በዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ አማካኝት በሚከተሉት ይዘቶች ላይ ስልጠናዎችን ያገኛሉ፡፡

  • ስለ ካፒታል ዕቃ ፋናንስ አገልግሎት ምንነትና ጠቀሜታዎች፣
  • የሊዝ ፋይናንስ ተጠቃሚዎች ማሟላት ስለሚገባቸው መረጃዎች አደረጃት፣
  • የኪራይና የብድር አገልግሎት ለማግኘት የሚጠቅሙ ወሳኝ የመመልመያ ነጥቦችና የጠራ መረጃ አደረጃጀት፣
  • የኪራይ አከፋፈል ምጣኔ እና የአከፋፈል ስርዓት አይነቶች፤
  • ከዚህ ባሻገር ማንኛውም በዘርፉ እየሰራ ያለ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆነ ሀገራቀፍና አለማቀፍ ተቋም በእነዚህ መስኮች ላይ ስልጠና የሚፈልግባቸው ማዕቀፎች ካለውና ስልጠናዎች እንዲሰጥለት ከፈለገ በጋራ ለመስራትና ድጋፍ ለማድረግ የምንችል መሆኑንም በዚህ አጋጣሚ ለማስገንዘብ እንሻለን፡፡

የተጠቃለለ ሪፖርት

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር በሰባት ባለአክሲዮኖች በተከፈለ ብር 400 ሚሊዮን ካፒታል የተቋቋመ ሲሆን አሁን ላይ ካፒታሉ ወደ ብር 552.89 ሚሊየን አድጓል። እስከ ሰኔ 30/2024 እ.ኤ.አ ድረስ ብቻ 2,415 አክቲቭ ደንበኞች የካፒታል ዕቃ አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ አዲስ አበባን ጨምሮ በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች 27 ቅርንጫፎችና በስራቸው በሚገኙ በ187 ሳተላይት ጽ/ቤቶች አማካኝነት በአጠቃላይ በ214 ከተሞች ላይ አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል።

ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ ሀብቱ 1.6 ቢሊየን ብር በላይ ሲደርስ ካፒታሉ ደግሞ 552.89 ሚሊየን ብር ደርሷል፤ ይህም በሀገሪቱ ውስጥ ከተቋቋሙት አምስት የሊዝ ኩባንያዎች መካከል ሰፊውን የሊዝ ገበያ እንዲይዝ አድርጎታል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ ከተቋቋመበት 2007 ዓ.ም ጀምሮ 16,045 የካፒታል ዕቃዎችን 7,168 አንቀሳቃሾችን ላቀፉ 5,263 ተጠቃሚ ተከራዮች ዋጋቸው ብር 2,443,929,897.47 የሚሆኑ የካፒታል ዕቃዎችን አከራይቷል፡፡ የአገልግሎታችን ተጠቃሚዎች 5,535 ወንድ እና 1,633 ደግሞ ሴቶች ሲሆኑ በእነዚህ አንቀሳቃሾችም ከ33,364 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል።

በአጠቃላይ የአክሲዮን ማህበሩ ያለፉት አራት ዓመታት ለውጦችና ድምር ስኬቶቹ ሲታይ በየዓመቱ ከፍተኛ ዕድገት የሳየበት ነው፡፡ ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በክልሉ ውስጥ በተፈጠረው የሰላም እጡት እና የገንዘብ እጥረት በአፈፃፀሙ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል።

report

ዕቅድ እና ስትራቴጂ ጉዳዮች

ምንም እንኳ በኢትዮጵያ የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ገና በማደግ ላይ የሚገኝ ቢሆንም በተደረጉ ምክክሮችና አገልግሎቱን የማስተዋወቅ ተግባራት በካፒታል ዕቃ አቅርቦት መጠንም ሆነ ስፋት ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ የማደግ ዕድሉ እየሰፋ ነው። በአሁኑ ጊዜ አክሲዮን ማህበሩ በክልላችንም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ ደንበኞች ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ኢን/ዞች ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገሪቱ ባሉ ኩባንያዎች ጭምር የሊዝ ፋይናንስ አቅርቦት ገበያውንና የደንበኞችን ፍላጎት አሁንም ሊያረካ አልቻለም።

የአክሲዮን ማህበሩ ዋና ደንበኞች በማኑፋክቸሪንግ፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በግብርና እና በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች በማምረት ተግባራት ላይ የተሰማሩ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው። እነዚህ ኢን/ዞች በተለያዩ ደረጃ ማለትም በማደግ ላይ ያሉ ወይም በግል እየሰሩ የንግድ ስራቸውን እያስፋፉ ያሉ እንዲሁም ከጥቃቅንና አነስተኛ ወደ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ባለቤትነት የሚሸጋገሩ፣ የካፒታል ዕቃ/ማሽን እጥረት ያለባቸውና የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ሲሆኑ በየደረጃው ከሚገኙ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ተቋማት እንዲሁም በክልሉ የስራና ስልጠና ተቋማት የተያዙ መረጃዎች በመውሰድ እና ሌሎችም በራሳቸው የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ፈልገው የሚመጡ ናቸው።

  • የአክሲዮን ማህበሩ የረጅም እና የአጭር ጊዜ ዋና ዋና ግቦች እና የትኩረት አቅጣጫዎች፡-

የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ድርጅቶች ሥራቸውን እንዲያስፋፉ ያግዛል፤ ስለሆነም በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ የጥቃቅን፣አነስተኛ እና መካከለኛ ኢን/ዞች የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያው ግቡን እንዲመታ ተገቢውን ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገባቸው አቅሞች መካከል ዋነኞች ናቸው። ይህንን ለማድረግ ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር ፍላጎቱን ሊያሟላ የሚችል እና ይህንን ትልቅ አቅም ለመጠቀምና ኢንተርፕራይዞች ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሻገር የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያው ወደፊት እድል ሊሰጥ ይችላል።

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ በጥቃቅን፣አነስተኛ እና መካከለኛ ኢን/ዞች በተመረጡ ዘርፎች በዋናነት በማኑፋክቸሪንግ፣ በቱሪዝም፣ በግንባታ እና በሌሎች አገልግሎት እና በግብርና ዘርፎች ላይ ትኩረት በመስጠት የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ይሰጣል። የሊዝ ፍላጎት ያላቸውን አመልካቾች ፍጥነት መጨመር፣ የሰራተኞችን ሙያዊ ብቃት እና የሊዝ ፋይናንስ ዕውቀት ማሳደግ እንዲሁም የደንበኞችን ፍላጎት ማሟላት ቀጣይነት ያለው ሌላው የጥቃቅን፣አነስተኛ እና መካከለኛ ኢን/ዞች ስትራቴጂ አካል ነው።

ከአጭር ጊዜ ዕቅድ አንፃር ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር የተደራሽነት ሽፋንን ለመጨመር የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እና የሳተላይት ከተሞችን ተጠቃሚነት ማሻሻል አለበት። ማህበራዊ ሚዲያን (ድህረ ገጽ፣ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም የመሳሰሉትን እና የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ሊያሳልጡ የሚችሉ ሲስተሞችን በመጠቀም ወደ ደንበኞች ለመድረስ እና ለደንበኞች የሚቀርቡ አገልግሎት ለማሳለጥ (ለምሳሌ፡ የሊዝ ማመልከቻዎች፣ ደንበኞችን ለማወቅ/ለመመልመል የሚጠቅሙ መስፈርቶች (KYC) እና ሌሎች ሰነዶችን በእነዚህ መገናኛ ዘዴዎች መጫን፣ እንዲሁም የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ክፍያ በዲጅታል መንገድ እንዲፈጸም እና ሌሎች በርካታ የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎቶችን በተመለከተ ጥሩ አመለካከት እንዲኖር ማድረግና አጠቃላይ አገልግሎቱን ማሻሻል ነው፡፡

ከረጅም ጊዜ አንጻር አክሲዮን ማህበሩ በክልሉ የሊዝ ፋይናንስ ገበያውን ማርካት፣ አገልግሎቱን በሀገር ደረጃ ማስፋት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የኢንዱስትሪ ዘርፍን በመላ አገሪቱ ለማሳደግ እና በኢትዮጵያ ቀዳሚ የሊዝ ኩባንያ ለመሆን የረጅምና የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ዋና ዋና ግቦችና የትኩረት አቅጣጫዎች

በዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክሲዮን ማህበር በስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ የተገለጹት ግቦችና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች በሚከተሉት መልኩ ተለይተዋል፡-

  • የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ማስተዋወቅ እና ገበያውን ማስፋፋት (ከስትራቴጂክ ደንበኛ(ዎች) ጋር ጠንካራ አጋርነት እና ትስስር መፍጠር እና ማዳበር)፤
  • የሀብት ማሰባሰብ (የኩባንያውን አገልግሎት የሚያሻሽሉ አዳዲስ የንግድ ሞዴሎችንና የፋይናንስ ምንጮን መፍጠር እና መጠቀም)፤
  • የደንበኞች አገልግሎት ቅልጥፍና እና ልቀት ማሻሻል (ለደንበኞች የተሻለ እና እሴት የሚጨምር አገልግሎት በማቅረብ ስትራቴጂያዊ ችሎታ ማዳበር)፤
  • ድርጅታዊ መዋቀርና እና ሰራተኞች፤
  • የሊዝ ፋይናንስ አስተዳደር የመረጃ ስርዓት ማዘመን /አውቶሜሽን እና ዲጂታላይዜሽን)፤
  • የፋይናንስ አስተዳደር (የባለአክሲዮኖችን ኢንቨስትመንት ትርፋማ ማድረግ /መፍጠር)፤
  • የሪስክ አስተዳደር እና ተገዢነት ስርዓት መዘርጋት፤ ማሻሻል፤
  • ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን /ምርቶችን/ማቅረብ፤

ግቦች

  • አገልግሎቶች የሚሰጡባቸው መዳረሻዎች መጨመር እና የደንበኞችን ተደራሽነት ማስፋፋት (የደንበኛ እይታ)፤
  • ሀብትን ማሰባሰብ እና ትርፋማነትን ማሻሻል (የፋይናንስ እይታ)፤
  • የካፒታል ዕቃዎች አቅርቦትን ማሳደግ (የውስጥ አሰራር ሥርዓት እይታ)፤
  • የአገልግሎት ልዕቀት (የመማማርና ዕድገት እይታ) ማሳካት፤

ያግኙን

ዋና መስሪያ ቤት

ስልክ ቁጥር.+251 58 220 6780/ 58 220 6786

ፋክስ: +25158 220 5342 / 0583209918

ኢሜል:waliyacapital@gmail.com

የቅርንጫፎች አድራሻ

አዲስ አበባ ቅርንጫፍ +251 11 170 6079

ባህር ዳር ቅርንጫፍ +251 58 222 1443

ጣና ቅርንጫፍ +251 58 220 8444

ጎንደር ቅርንጫፍ +251 58 211 5023

ደብረ ማርቆስ ቅርንጫፍ +251 58 178 0135

ደሴ ቅርንጫፍ +251 33 312 3600

ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ +251 11 637 5084

እንጅባራ ቅርንጫፍ +251 58 227 1627

አዴት ቅርንጫፍ +251 58 338 1106

ቆቦ ቅርንጫፍ +251 33 334 1141

ደባርቅ ቅርንጫፍ +251 58 117 0554

ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ +251 33 851 4165

ወልድያ ቅርንጫፍ +251 33 331 2585

ፍኖተ ሰላም ቅርንጫፍ +251 58 775 0117

ደብረ ታቦር ቅርንጫፍ +251 58 141 0320

ሰቆጣ ቅርንጫፍ +251 33 540 0555

ከሚሴ ቅርንጫፍ +251 33 554 1221

ወረታ ቅርንጫፍ +251 58 446 1341

መካነኢየሱስ ቅርንጫፍ +251 58 447 0219

ቻግኒ ቅርንጫፍ +251 58 225 0583

ቡሬ ቅርንጫፍ +251 58 774 1015

ቢቸና ቅርንጫፍ +251 58 665 1621

ገንዳ ውሃ ቅርንጫፍ +251 58 331 0699

ጋሸና ቅርንጫፍ +251 33 443 0734

ሸዋ ሮቢት ቅርንጫፍ +251 33 664 1936

አቀስታ ቅርንጫፍ +251 33 814 1937

መሀል ሜዳ ቅርንጫፍ +251 11 685 0733

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችና መስፈርቶች ምንድን ናቸው ?

ቢሯችሁ የት ነው የስልክ አድራሻም ብትሰጡን ?

የምትሰጧቸውም አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው ?

ማሽን አቅራቢዎችን እና የማሽን ዋጋ እዴት ማግኘት ይቻላል ?

ለስራ የሚያስፈልጉንን መሰረተልማቶች በተለይ የስራ ቦታ እና የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲሟላልን አድርጉልን?

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች እና መልሶች

ኢንተርፕራይዞች አገልግሎቱን ለማግኘት ማሟላት የሚገባቸው መሰፈርቶች እና ቅድመ ሁኔታዎች

በአክሲዮን ማህበሩ አገልግሎቶች ላይ ሙሉ ግንዛቤ ያላቸው፤

ስለሚጠይቁት መሳሪያ አጠቃቀም በቂ ክህሎት/ግንዛቤ ያላቸው

እንዲገዛ የሚጠየቀው የካፒታል ዕቃ የገንዘብ መጠን ከ25 ሽ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ብቻ የሆነ፤

የንግድ ስራ ዕቅድ /Business Plan/፤ ለትልልቅ ፕሮጀክቶች ፕሮፖዛል ማቅረብ የሚችሉ፤

ለሚገዛላቸው ማሽን ዝርዝር መግለጫ /Specification/ የሚያቀርቡ፤

እንዲገዛላቸው የሚፈልጉትን የካፒታል ዕቃ ጥቅል ዋጋ ከ20 እስከ 50 በመቶ ቅድመ ቁጠባ መቆጠብ የሚችሉ፤

የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤

መሰረተልማቱ የተሟላ በቂ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ያላቸው

ከአበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት የመልካም ተበዳሪነት ታሪክ ያላቸው፤

ለነባር ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ መዝገብ ያስመረመሩ፤ አዲስ ከሆኑም ለማስመርመር ፍቃደኛ የሆኑ፤

ለሚቀርብላቸው መሳሪያ የመድህን ሽፋን (የጉዞ እና የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ) የሚገቡና በየአመቱ ለማሳደስ ፈቃደኛ የሆኑ፤

መሳሪያውን በውል ለማስመዝገብ ፈቃደኛ የሆኑ፤

መሳሪያውን የሚንከባከቡና ብልሽት ሲያጋጥም የሚያስጠግኑ እንዲሁም ጥበቃ የሚያደርጉ፤

የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ያላቸው /ብድር ማግኘት የሚችሉ፤

የጋብቻ ሁኔታን (ያገቡ /ያላገቡ) የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ

በሚኖሩበት ቀበሌ/ክፍለ ከተማ/ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

ቅድሚያ በሚሰጣቸው የስራ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ኢንተርፕራይዞች ከሆኑ በፈጻሚ አካላት በጋራ ተመልምለው የማምረቻ መሳሪያ ኪራይ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

ቢሮዎቻችን እና አድራሻችን

ዋና መስሪያ ቤት

ስልክ ቁጥር.+251 58 220 6780/ 58 220 6786

ፋክስ: +25158 220 5342 / 0583209918

ኢሜል:waliyacapital@gmail.com

የቅርንጫፎች አድራሻ

አዲስ አበባ ቅርንጫፍ +251 11 170 6079

ባህር ዳር ቅርንጫፍ +251 58 222 1443

ጣና ቅርንጫፍ +251 58 220 8444

ጎንደር ቅርንጫፍ +251 58 211 5023

ደብረ ማርቆስ ቅርንጫፍ +251 58 178 0135

ደሴ ቅርንጫፍ +251 33 312 3600

ደብረ ብርሃን ቅርንጫፍ +251 11 637 5084

እንጅባራ ቅርንጫፍ +251 58 227 1627

አዴት ቅርንጫፍ +251 58 338 1106

ቆቦ ቅርንጫፍ +251 33 334 1141

ደባርቅ ቅርንጫፍ +251 58 117 0554

ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ +251 33 851 4165

ወልድያ ቅርንጫፍ +251 33 331 2585

ፍኖተ ሰላም ቅርንጫፍ +251 58 775 0117

ደብረ ታቦር ቅርንጫፍ +251 58 141 0320

ሰቆጣ ቅርንጫፍ +251 33 540 0555

ከሚሴ ቅርንጫፍ +251 33 554 1221

ወረታ ቅርንጫፍ +251 58 446 1341

መካነኢየሱስ ቅርንጫፍ +251 58 447 0219

ቻግኒ ቅርንጫፍ +251 58 225 0583

ቡሬ ቅርንጫፍ +251 58 774 1015

ቢቸና ቅርንጫፍ +251 58 665 1621

ገንዳ ውሃ ቅርንጫፍ +251 58 331 0699

ጋሸና ቅርንጫፍ +251 33 443 0734

ሸዋ ሮቢት ቅርንጫፍ +251 33 664 1936

አቀስታ ቅርንጫፍ +251 33 814 1937

መሀል ሜዳ ቅርንጫፍ +251 11 685 0733

የምንሰጣቸው አገልግሎቶቻች/ምርቶቻች

የዱቤ ግዥ ኪራይ

የፋይናንስ ኪራይ

የስልጠና አገልግሎት

የማማከር አገልግሎት

ማሽን አቅራቢዎችን እና የማሽን ዋጋን በተመለከተ

የአክሲዮን ማህበሩ ተግባር በሊዝ ለሚቀርቡ ማሽኖች ፋይናንስ ማድረግ ሲሆን ወደኛ ከሚመጡ ኢንትርፕራይዞች ደግሞ የተሰማሩበትን ወይም የሚሰማሩበትን ስራ በደንብ ማወቅ የሚጠበቅ ቅድመሁኔታ ነው፡፡ ስለሆነም ደንበኞች የሚፈልጓቸውን መሳሪያዎች አይነትና ባህሪ እንዲሁም የሚገኙበትን ቦታና ዋጋቸውን በደንብ ማጥናትና ማወቅ አለባቸው ማት ነው፡፡ የእኛ ተቋም ሙያዊ እገዛ ካስፈለገ በግዥው ሂደት ላይ እንዳስፈላጊነቱ እገዛ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ለስራ የሚያስፈልጉንን መሰረተልማቶች በተለይ የስራ ቦታ እና የኤሌክትሪክ ሀይል በተመለከተ

አገልግሎታችንን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች በግልጽ እንዳስቀመጥነው ማንኛውም ኢንተርፕራይዝ ወደ እኛ ሲመጣ መሰረተልማቱን አሟልቶ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን የመሳሪያ ወይም የማሽን መግዣ ገንዘብ እጥረት ቢኖርበት ወይም ያለችውን ለስራ ማስኬጃ ቢፈልጋት ከእኛ ያለምንማ ተጨማሪ ማስያዣ/ዋስትና የሚፈልጋቸውን ማሽኖች በሊዝ ፋይናስ ስርዓት መውሰድ ይችላል፡፡ የእኛ ተቋም ኢንትርፕራይዙ ለብድሩ ተጨማሪ ማስያዣ ከሌለው ከሌሎች የፋይናስ ተቋማት ብድር ማግኘት ላያገኝ ስለሚችል አይነተኛ መፍትሄው ይሆናል፡፡ ስለሆነም የመሰረተልማት ጉዳይ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ማለቅ ያለበት ጉዳይ ይሆናል ማለት ነው፡፡

መሰፈርቶች እና ቅድመ ሁኔታዎች

ኢንተርፕራይዞች አገልግሎቱን ለማግኘት ማሟላት የሚገባቸው መሰፈርቶች እና ቅድመ ሁኔታዎች

  • በአክሲዮን ማህበሩ አገልግሎቶች ላይ ሙሉ ግንዛቤ ያላቸው፤
  • ስለሚጠይቁት መሳሪያ አጠቃቀም በቂ ክህሎት/ግንዛቤ ያላቸው
  • እንዲገዛ የሚጠየቀው የካፒታል ዕቃ የገንዘብ መጠን ከ25 ሽ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ብቻ የሆነ፤
  • የንግድ ስራ ዕቅድ /Business Plan/፤ ለትልልቅ ፕሮጀክቶች ፕሮፖዛል ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ለሚገዛላቸው ማሽን ዝርዝር መግለጫ /Specification/ የሚያቀርቡ፤
  • እንዲገዛላቸው የሚፈልጉትን የካፒታል ዕቃ ጥቅል ዋጋ ከ20 እስከ 50 በመቶ ቅድመ ቁጠባ መቆጠብ የሚችሉ፤
  • የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  • መሰረተልማቱ የተሟላ በቂ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ያላቸው
  • ከአበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት የመልካም ተበዳሪነት ታሪክ ያላቸው፤
  • ለነባር ኢንተርፕራይዞች የሂሳብ መዝገብ ያስመረመሩ፤ አዲስ ከሆኑም ለማስመርመር ፍቃደኛ የሆኑ፤
  • ለሚቀርብላቸው መሳሪያ የመድህን ሽፋን (የጉዞ እና የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ) የሚገቡና በየአመቱ ለማሳደስ ፈቃደኛ የሆኑ፤
  • መሳሪያውን በውል ለማስመዝገብ ፈቃደኛ የሆኑ፤
  • መሳሪያውን የሚንከባከቡና ብልሽት ሲያጋጥም የሚያስጠግኑ እንዲሁም ጥበቃ የሚያደርጉ፤
  • የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ያላቸው /ብድር ማግኘት የሚችሉ፤
  • የጋብቻ ሁኔታን (ያገቡ /ያላገቡ) የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ
  • በሚኖሩበት ቀበሌ/ክፍለ ከተማ/ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ቅድሚያ በሚሰጣቸው የስራ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ኢንተርፕራይዞች ከሆኑ በፈጻሚ አካላት በጋራ ተመልምለው የማምረቻ መሳሪያ ኪራይ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

ባለድርሻ አካላት

ዋልያ የካፒታል ዕቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አ.ማ ሶስት መሰረታዊ ተግባራትን ማለትም የሀብት ማሰባሰብ፣ የመሳሪያ ግዥ እና የመሳሪያ ኪራይን ሲያከናውን ቆይቷል። የኩባንያው ሶስት ዋና ዋና ተግባራትን እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ግንኙነት ተለይተዋል፤ ይህም ከታች ባለው ምስል ተገልጿል፡፡

    ውስጣዊ

  • የተቋሙ የዳይሬክተሮች ቦርድ (ባለቤቶች /ባለአክሲዮኖች)
  • የተቋሙ ስራ አመራር
  • የተቋሙ ሰራተኞች

    ውጫዊ

  • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
  • ደንበኞች/ተከራይ ኢንተርፕራይዞች
  • አቅራቢዎች/አምራቾች ድርጅቶች
  • አበዳሪ ተቋማት
  • የፌደራልና የክልል እንዲሁም የከተማና የወረዳ አስተዳደሮች
    • የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት
    • ኢንዱስትሪ ሚንስቴር
    • የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ
    • ጸደይ ባንክ አ.ማ
    • የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ
    • የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ
    • የአብክመ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
    • የአብክመ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ እና በየደረጃው ያሉ መዋቅሮቻቸው

በባለድርሻ አካላት ትንተና ላይ በመመስረት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ውስጥ ዋና ዋና አካላት የሚባሉተ ፋይናንስ ሰጪ ፣ ተከራይ ፣ አከራይ እና አቅራቢ ናቸው። ከላይ ያለው ሥዕል የእነዚህን ወገኖች ግንኙነት ያሳያል፡፡

coaster Bid
image board meeting
image board meeting agenda